The United States Census of 2020

የህዝብ ቆጠራው ለምንድነው አስፈልጊ የሚሆነው?
በቁጥር ብዛት ጥንካሬ አለ:: በዚህ አካባቢ የምንኖር የኢትዮጵያ ዘር ሃረግ ያለን ነዋሪዎች ከአመት አመት ቁጥራችን እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው:: በዚህ የህዝብ ቆጠራ መሳተፋችንና በቤታችን የኢትዮጵያ ዘር ሃረግ ያለው ሰው የኢትዮጵያ ዘር ሃረግን ምርጫ በመሙያው ላይ መምረጥ በጣም አስፈላጊ ነው:: እንደዚህ አይነት መረጃ የመንግስትን የገንዘብ አሰረጫጨት በኛና በልጆቻችን የወደፊት ህይወት ላይ ዐስተዋፅኦ የሚያመጡ እንደ ሚከተሉት ያሉ አገልግሎቶች ላይ ተፅዕኖ አለው::
በተጨማሪም የሁላችንም ተሳትፎ የኢትዮጵያን ህበረተሰብ በአካባቢያችን የፖለቲካ መሪዎች ተደማጭነተን ያሰጣል:: በዚህ የህዝብ ቆጠራ መሳተፋችን የቁጥራችንን ብዛት ለአካባቢያችን መሪዎች ስለሚያሳይ እና መሪዎች ምርጫ ላይ ልዩነት እንደሚያመጣ ስለሚገነዘቡ ለህበረተሰባችን ትኩረት ያሰጣል::
-
ለትምህርት ቤቶች
-
(ነፃ ቁርስና ምሳ)
-
የተለየ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች
-
-
ለመጸሐፍት ቤቶች
-
ለጤና
-
የመንግስት ቤት እርዳታ (Section 8)
-
ማህበረሰብን ለሚያገለግሉ ተቓማት እርዳታ (Community services)
-
መንገድ ግንባታ
ጥያቄ :ቁጥር: 9
የዘር ሐረግን ይጠይቃል:: እርስዎና ቤተሰብዎ ኢትዮጵያዊ ማለትን እንዳይረሱ:: በቁጥር ብዛት ጥንካሬ አለ:: ተፅእኖ ማምጣትም ይቻላል::

የህዝብ ቆጠራው ለምንድነው አስፈልጊ የሚሆነው?
የህዝብ ቆጠራው ብዙ የተለያዩ የህይወትዎ መስኮችን ፈር ለማስያዝ የሚያስችል ወሳኝ መረጃዎችን ይሰጣል። ሕግ አውጪዎች የንግድ ስራ ባለቤቶች አስተማሪዎች እና ሌሎች ብዙ አካላት ይህን መረጃ በየቀኑ አገልግሎቶችን ምርቶችን እና ማህበራዊ ድጋፍን ለመስጠት ይጠቀማሉ ።
እንዴት እገዛ ማድረግ ይችላሉ?
መረጃን ማሰራጨት
ህዝብ ቆጠራ ቢሮ ዜና እና መረጃ ለጓደኞችዎ ቤተሰቦችዎ፣ የፌስቡክ ትዊተር እና ኢንስታግራም ተከታዮችዎ በማጋራት ሊረዱን ይችላሉ።
ግላዊነት እና ደህንነት?
እርስዎ የሚሰጡዋቸው መልሶች የስታትስቲክስ ግብዓቶችን ብቻ ለማዘጋጀት የሚውል ነው።
ለተጨምሪ መረጃ ይሚከተሉትን ሊንከ (click the following links) ይጎብኙ
ለ 2020 ህዝብ ቆጠራው እንዴት ምላሽ መስጠት አለብዎ?
የ 2020 የህዝብ የቆጠራ መመሪያ
ይህ ፕሮጀክት በከፊል ከሲሊከን ቫሊ ማህበረሰብ ፋውንዴሽን እና ከዩናይትድ ዌይ ቤይ ኤርያ በተገኘ ገንዘብ የተደጋፈ ነው ::



